10 Comments
User's avatar
Mak Habesha's avatar

ይሄ ጉዳይ ከተነሳ ተጨማሪ ምርመራና ዘገባ ያስፈልገዋል ይሄ ብቻ አይደለም ። እኔ እምሰራበት ባንክ ለ ድስትሪክትና ለ ዋናው መስሪያቤት ከፍተኛ ኃላፊዎች እስከ ብር 20,000,000.(ሀያ ሚሊዮን) የሚደርስ አድቫንስ ተፈቅዶላቸው አድስ አበባ ላይ ቤት ያልገዛ ችፍ ዳይሬክተርም ሆነ የድስትሪክት ኃላፊ የለም። ከዚህ በተጨማሪም አስመጪና ላኪ እስከመሆን የደረሱ አሉ በሽንኩርትና መሰል የግብርና ዘርፎችም ኢንቨስት እስከማድረግ የደረሱ አሉ። ይህ ሁሉ እሚሆነው የቅርንጫፍ ሰራተኞች በሚሰበስቡት የደንበኞች ተቀማጭ ገንዘብ ነው። በዛ ላይ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች በስራቸው ያለን ሰራተኛ ስም ማጉደፍም ሆነ ማሳመር ይችላሉ። የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጁ ያልተመቸውን ወይም በግሉ እሚጠላውን ሰራተኛ በ 1 ደብዳቤ ብቻ ለድስትሪክቱ በመላክ ማስባረር ሁሉ ይችላል። ይህ ሁሉ እሚሆነው አሁን ባለሁበት ባንክ በተለይም ደግሞ ደሴ ድስትሪክት ነው። ሌሎችም ተጨማሪ ጉዳዮች አሉ email አደርጋለሁ።

Expand full comment
Sisay's avatar

እኔን ከጎንደር ወደ አይራ ጎሊሶ ሲያዛውሩኝ፣፣ስራ ለመልቀቅ ተገደድኩ ፣ ያለብኝን የባንክ እዳ ለመዝጋት ቤቴን ሽጭ ኪራይ ላይ ነኝ ከ 3 ልጆቼ ጋር ።

Expand full comment
Sisay's avatar

ይህን ያደረገው አዋሽ ባንክ በወቅቱ በተመሳሳይ ጉደይ ብዙ ለቋላ አንዷ አራስ ነበረች

Expand full comment
Nigus's avatar

በጣም ያሳዝናል።😥

Expand full comment
Asresie Abate's avatar

የሁላችንም ጥያቄ ቢሆንም ነገር ግን መፍትሄ ያጣ ጉዳይ ነው።በተለይ ሴት ሰራተኞች ደንበኛ ሲያጡ በግድ ህሊናው ባዶ እና እጅግ ከቆሸሸ አስተሳሰብ ካለው የገንዘብ ሀብታም ጋር ያለፍላጎታቸው ስጋቸውን እና ትዳራቸውን አርክሰው (ተገደው) ወሲብ እንዲፈፅሙ ከስራ አስኪያጁ ጀምሮ ትዛዝ ይሰጣቸዋል ያን ካላደረጉ ከቤተሰብጨርቀው ሪሞት ቦታዎች ትመደባላቹ ሌሎች ጥቅማጥቅሞችም እንደሚቀነሱ ይነገራቸዋል ብሎም ተግባራዊ ይደረግባቸዋል።በዚህ ምክንያት ስንት የሞቀ ትዳር ተበትኗል መሰለህ ወንድሜ።ባለሀብቱ ገንዘብ እንዲቆጥብ ለማስማማት ስራ አስኪያጆች ሁሉንም ሰራተኞች ያለፈቃዳቸው በባለሀብቱ ፈቃድ ለወሲብ የሚረከዙ ሲሆን ያን አላደርግም የሚል ሰራተኛ እንጦረንጦስ የሆነ ቦታ ሊመደብ ከመደብ ዝቅ እና ለሌሎች ያልተገቡ ተግባራትም ይጋለጣል።ብቻ ተዘርዝሮ አያልቅም።በቂ ማስረጃ ከመረጃ ማቅረብ ከፈለክ እኔ ጋር አለ ደህንነቴ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ እንጂ

Expand full comment
Baba's avatar

አረ ልክ ናቸው። እኔማ ከሆነ ጊዜ ወዲህ መንገድ ላይ አባት አባት፣ ወንድም ወንድም፣ የሚል ድምጽ በሰማሁ ቁጥር ከአሁን አሁን አካውንት ክፈት ሊሉኝ ነው በቃ ብዬ እየተሳቀቅኩ ነው። ደሞ ከሌለኝ ብር ላይ ቀፍለውኝ አካውንት ማስከፈታቸው ሳይበቃ፣ እንደማንኛውም ደንበኛ ገንዘቤን እንዳሻኝ ለማንቀሳቀስ ATM ካርድ እና የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት እንዲሰጡኝ ስጠይቃቸው ለደህንነትህ አስጊ ስለሆነ ለዐይነስውራን እነዚህን አገልግሎቶች አንሰጥም ብለውኝ ያርፉታል። ይሄ ጉዳይ በተለይ በግል ባንኮች በኩል ይብሳል። የውጪ ባንኮች በመጡና በገላገሉን አቦ።

Expand full comment
MICHAEL's avatar

በቅርብ ሁለት ሱፍ የለበሱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ቢሮ አንኳኩተው ገቡ። በሰዓቱ ከአንድ ቀደም ሲል ቀጠሮ አስይዞ ከመጣ እንግዳ ጋር ውይይት ላይ ነበርኩ። በመሃል ተነስቼ በር ከፈትኩ። ከገቢዎች ወይም ከንግድ ቢሮ ይሆናሉ ብዬ ስላሰብኩ ወንበር ስቤ እንዲቀመጡ ጋበዝኳቸው። ወዲያው ስለ ድርጅታችን እና ስለምንሰራው ስራ ጠየቁን። እኔም ቀደም ሲል የነበረኝ ጥርጣሬ እውነት መስሎኝ ማብራራት ጀመርኩ። እናንተስ ከየት መጣችሁ ስል አንደኛው ከባንክ ነው አለ። አስቡት የአንድ ባንክ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ነው። አመጣጣቸው አካውንት ለማስከፈት ነበር።

Expand full comment
Yonas Negusie Ayele's avatar

This is an excellent piece. Based on this report, I wrote a blog post titled: "Can You Squeeze Water from a Stone"; that tackles the growing crisis in Ethiopia's private banking sector. As noted in your report, employees are facing immense pressure and unrealistic deposit targets amidst challenging economic conditions.

The current approach is unsustainable. It's time for a digital-first strategy to drive inclusive growth, as demonstrated by platforms like Telebirr and Kenya's banking sector.

Read why this shift is crucial: https://poweredupyonasnegusie.substack.com/p/can-you-squeeze-water-from-a-stone

Demeke Alamirew's avatar

እኔ ሳላመለከት እኔ በማላውቀው ሁኔታ ሞባይል ባንኪንግ አስጀምረውኝ አግኝቻለሁ። 3 ወር በላይ ካልተጠቀምኸው ደሞ ሲስተሙ ያቆማል። ከዓመት በኋላ የካሽ እጥረት ስላለ ብዙ ባንኮች አካውንት መክፈት ግድ ሆነብኝ። ያን ቀድሞ የከፈትሁትን ደግሞ ሞባይል ባንኪንግ ማስጀመር ፈለግሁኝ። ግን ተከፍቶበታልኮ አዲስ አይቻልም አሉኝ። ስህተት ይሆናል ብዬ አካውንት የከፈትሁበት ቅርንጫፍ ሳስደውልም ጀምሮ ሳይጠቀምበት 3 ወር ስላለፈው ሌላ አካውንት ካልከፈተ በቀር በዚህ አካውንት ሞባይል ባንኪንግ መጠቀም አይችልም ተባልሁ። አቢሲኒያ ባንክ ደብረ ማርቆስ ቅርንጫፍ።

Expand full comment