'መሠረት ሚድያ ላይ subscription ለምን አስፈለገ?'- በመሠረት ሚድያ ኤዲተር ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት
(መሠረት ሚድያ)- ሚድያችን ስራ ከጀመረ ጀምሮ ያለውን ተፅእኖ፣ ጥቅም እና አቅም የተረዱ በርካታ አካላት (ግለሰቦች እና ተቋማት) በሼር አብረን እንስራ እና ሌሎች ጥያቄዎች አቅርበው ነበር።
ይሁንና ሚድያ በፀባዩ ነፃ እና ገለልተኛ መሆን ስላለበት እና እነዚህ ጥያቄዎች ወደፊት በዜናዎቹ ላይ ሊፈጥሩ የሚችሉት የጥቅም ግጭት እና ተፅእኖ ስለማይታወቅ አልተፈለገም።
ሚድያችን በአብዛኛው የህዝብ ድምፅ ላይ አተኩሮ ስለሚሰራ ንብረትነቱንም የህዝብ ማድረግ የሚለው የተሻለ አማራጭ ሆኖ ተገኝቷል፣ በዚህም መሠረት የ subscription አገልግሎት ተጀምሯል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉት ከ80 ፐርሰንት በላይ ለሚሆኑት አንባቢዎቻችን በጥቂት ክፍያ በቴሌብር ወይም ኤምፔሳ አገልግሎቱን ማስጀመር ብንችልም በመንግስት በኩል የሚገጥመንን ተግዳሮት መገመት ይቻላል፣ ግን ሌሎች አማራጮችን ማየት እንቀጥላለን። እስከዛው አንዳንድ ዜናዎችን በነፃ እንለቃለን።
ላለፉት ስምንት ወይም ዘጠኝ ወራት በግሌ ለሁለት ሪፖርተሮች ክፍያ በመፈፀም፣ ባለኝ ትርፍ ግዜ 20 ገደማ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር እና ራሴ የበጎ ፈቃደኛ ኤዲተር በመሆን አገልግያለሁ። አሁን መሠረት ሚድያ የህዝብ መሆኛው ግዜ ደርሷል፣ ስለዚህ paid subscription ያላደረጋችሁ በማድረግ መሠረት ሚድያን ተረከቡኝ።
ሚድያው ጥሩ ሰርቷል፣ ለህዝብ እና ለሀገር ጠቅሟል ያላችሁ ቤተሰብ ሁኑ። አይ፣ ጥሩ አልሰራም የምትሉ ደግሞ subscribe ባለማድረግ ቅጡት።
አብዛኛው Free Trial Subscribers ቢሆኑም እስካሁን ከ3,400 በላይ ሰዎች ቤተሰብ ሆነዋል፣ በመሠረት ሚድያ ስም ከፍያ ያለ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
ኤልያስ መሠረት




በርታ ወዳጃችን