Discussion about this post

User's avatar
Kassa Ali's avatar

ልክ ነው ብልጽግና ለሀገር የሚጠቅም ሀሳቦችን በማፈን ሀገርን ወደ ለየለት ጥፋት ይዞ እየሄደ ነው። እንኳን እየሆነ ያለውንና በመረጃ የተደገፈውን መረጃ ወደ ፊት ሊሆን ይችላል ያለውን ማንኛውንም ሀሳብ ማራመድ መብት እንጅ ወንንጀል አልነበረም።

ብዙ ሚዲያዎች በተለይ የመንግስት የህዝብን ሀብት ሲቀልዱበትና ትኩረት ሊረጣቸው የሚገቡና የመንግስት ህጸጽ የሆኑ የሀገር አደጋዎችን አይተው እንዳላዩ ትንንሽ ስራዎችን እያጋነኑና በደጋፊዎቻቸው እያዘመሩ ሚዲውን እንዲንጠላ አድርገውናል። ለአብነት አባይና አሻም በሀገራችን እየሆነ ያለውን ጥፋት አፈንፍነው ሲዘግቡ አስቆሙ በግለሰብ ደረጃ የሚሞግቱ ታሰሩ።

እንደግለሰብ ጉዳት ደርሶባቸው ይሆናል ግና የሚበልጠው የሀገር ጉዳት ነው። የሀገርን ህጸጽ ማውሳትና መሞገት ለሀገር እድገትና ከስህተት ለማረም ትልቅ አቅም ነበር። እናም ሀገር የሀሳብና ነጻ ታጋይ ማጣቷ ወደ ቀውስ እንዲታመራ የሚጋብዝ አደገኛ አካሄድ ነው።

ፖለቲከኞቻችን በመንግስት ጥላ የተከለሉት አደባባይ የተሰጣውን ህዝብ በመዋሸት ሀገር የሚያሻግሩ ይመስላቸዋል። በየትኛውም መንገድ የተቃወመን ማጥፋት መፍትሄ መስሏቸዋል። ግና የሚቃወማቸውን ሊማሩበትና ስህተታቸውን ቢያርሙ ሀገራቸውን የበለጠ ከከፋ ችግር በታደጉ ነበር።

እኔ በበኩሌ በጠንካራ ትችታቸው የታሰሩ ልሂቃን እነሱ ሳይሆኑ ሀገራችን እንደታፈነች ነው የምቆጥረው። እናም አፈናው ለራሱ ለመንግስት አደገኛ የተደበቀ ፈንጅ ነው። ብልጥ ከሆነ ልሂቃኑን ፈቶ ሀሳባቸውን ወደ መድረክ ማምጣትና መወያየት መማማር ነው እሚጠቅመው።

Ahmed's avatar

The question is who is the 'journalist'?

No posts

Ready for more?