(መሠረት ሚድያ)- በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩት ፖለቲከኞቹ አቶ አበበ አካሉ እና ይሳቅ ወልዳይ እንዲሁም ጠበቃ አበራ ንጉሥ እያንዳንዳቸው በ50 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት መወሰኑ ተሰምቷል።
ፖሊስ በጠየቀው የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ላይ ትላንት ሐሙስ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም. ክርክር ከተደረገ በኋላ ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ለዛሬ አርብ ቀጥሮ ሰጥቶ እንደነበር የችሎች ምንጮች ለመሠረት ሚዲያ ተናግረዋል።
ትናንት ፖሊስ 14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው በጠየቀበት ወቅት በፖሊስ እና በተጠርጣሪዎች እንዲሁም በጠበቃቸው አማካይነት ከፍተኛ ክርክር የተደረገ ሲሆን በዚህም ክርክር የጥርምር ኃይሎች አመራሮች ስም ተነስቶ ነበር፡፡
እንደ ችሎት ተከታታይ ምንጮች ፖሊስ እነ ጠበቃ አበራ ንጉሱን ከፍተኛ ከሆኑ የህወሓት እና የጽምዶ አመራሮች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው፣ ለዚህም መረጃ አለን ማለቱ ታውቋል።
ከተጠርጣሪዎች መካከል ጠበቃ አበራ ንጉሱ በበኩላቸው "ፖሊስ ከፍተኛ ከሆኑ የህወሓት እና የጽምዶ አመራሮች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው ብሎ ያለው ወይ ከዶ/ር ደብረጺዮን ነው ወይም ከዘመነ ካሴ ጋር ነው፣ ስለዚህም ከእነዚህ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያደረግን ከሆነ ማስረጃ ካለው ቀጥታ ክስ መመስረት ነው እንጅ ለተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መጠየቂያ ምክንያት አይሆንም" በማለት የመለሱ መሆኑን ችሎት ሲከታተሉ ከነበሩ ምንጮች መሠረት ሚዲያ መረጃ አግኝቷል።
በዚህም መሰረት ጉዳዩን በመከታተል ላይ የሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የፖሊስን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ እያንዳንዳንዳቸው ተጠርጣሪዎች የ50 ሺህ ብር ዋስ አስይዘው እንዲፈቱ መወሰኑን ሰምተናል።
ጉዳዩን በመከታተል ላይ የሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የፖሊስን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ እያንዳንዳንዳቸው ተጠርጣሪዎች የ50 ሺህ ብር ዋስ አስይዘው እንዲፈቱመወሰኑን ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ጠበቃውእንደገለፁት ፍርድ ቤቱ ባለፈው ችሎት "የመጨረሻ" ያለውን የአንድ ሳምንት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ነበር ለፖሊስ የሰጠው።
ሆኖም የፌዴራል ፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ እንዲሰጠው ለችሎቱ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ባቀረበው ማመልከቻ ጠይቋል።
እስከነሐሴ 28/2018 ዓ.ም በተሰጠው ጊዜ ውስጥ የስድስት ሰዎችን የምስክርነት ቃል መቀበሉን ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነትአ ገልግሎት የፎረንሲክ ማስረጃዎችን ማስመጣቱን እንዲሁም ከ11 ባንኮች እና ከመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጠየቃቸውን ማስረጃዎች መቀበሉን ፖሊስ ገልጿል።
በተጨማሪም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ ዙሪያ ወረዳ በሚገኙ የዘይሴ ብሔረሰብ ቀበሌዎች ውስጥ ተጠርጣሪዎቹ ባደራጁት ታጣቂ ኃይል ተገድለዋል ስላላቸው 23 ንፁኃን ዜጎች እና ስለደረሰው ጉዳት የማጣራት ሥራ ማከናወኑንም አስታውቋል።
| መሠረት ሚድያ |
Discussion about this post
No posts


