ትግራይ ውስጥ ባሉ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ትንታኔ በማቅረብ የሚታወቀው ወጣት ሸዊት ውዳሴ በክልሉ የፀጥታ አባላት ተወስዶ መታሰሩ ታወቀ
(መሠረት ሚድያ)- የፖለቲካ ተንታኝ እና ትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው የሳልሳይ ወያነ ፓርቲ አባል የሆነው ወጣት ሸዊት ውዳሴ በፀጥታ አካላት ከትናንት በስቲያ ሀሙስ ከመቐለ ከተማ ተይዞ መወሰዱ ታውቋል።
'ሮማናት ኦንላይን' የሚል ፖድካስት አዘጋጅ የሆነው ሸዊት በቅርብ ግዜያት ሕወሓት እና የፖለቲካ አመራሮች ላይ የሰላ ትችት ሲያቀርብ የነበረ ሲሆን እስሩም ከእሱ ጋር የተያያዘ መሆኑን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ሸዊት ከእስር እንዲፈታ ዘመቻ የጀመሩ ሲሆን የክልሉን አመራሮች እና ባለስልጣናት የህዝብን ድምፅ በማፈን እየከሰሱ ይገኛሉ።
የመቐለ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆነው ሸዊት እስር በትግራይ ክልል ያለውን ለተለየ አስተሳሰብ ያለን ፍራቻ እና አንባገነናዊ አስተዳደር እንደሚያሳይ ጠቅሰው እየተቹ የሚገኙት የክልሉ ተወላጆች ወጣቱ በአስቸኳይ እንዲፈታ ወይም ህግ ፊት እንዲቀርብ ጠይቀዋል።
-መሠረት ሚድያ-


