ዛሬ ማምሻውን መቀሌ ከተማ ውስጥ ከባድ የፍንዳታ ድምፅ መሰማቱን ነዋሪዎች ተናገሩ፣ ነዋሪዎች ምን አሉ?
(መሠረት ሚድያ)- በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ፖለቲከኞች መሀል እየተካረረ የመጣው ውዝግብ በቅርቡ ወደ ግጭት ተቀይሮ የአውሮፕላን በረራ እስከ መቋረጥ መድረሱ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎ አለም አቀፍ ተቋማት እና አህጉራዊ ተቋማት ችግሩ በሰላማዊ መልኩ እንዲፈታ እያሳሰቡበት ባለበት በዚህ ወቅት ዛሬ ምሽት 3:35 ገደማ ያልተለመደ ከፍተኛ የፍንዳታ ድምፅ መቀሌ ከተማ ውስጥ መሰማቱን ነዋሪዎች ለመሠረት ሚድያ ተናገረዋል።
'ዳግም አምሳል' በተባለ ስፍራ ፍንዳታው እንደተከሰተ ነዋሪዎች ተናግረው የድሮን ጥቃት ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል።
ሌላ ምንጫችን ግን ፍንዳታው የቦንብ/ፈንጂ እንደሆነ መስማቱን እና ጥቃቱ የተፈፀመው ፍስሀ ማጁስ ተብሎ በሚጠራው የክልሉ ሀላፊ ቤት አካባቢ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህ ፍንዳታ ዙርያ እስካሁን በትግራይ አመራሮችም ሆነ በፌደራል መንግስት የተባለ ነገር የለም፣ ሚድያችን ተጨማሪ መረጃዎችን ይዞ ይመለሳል።



