ብዙዎችን እያጉላላ የሚገኘው የኢሚግሬሽን ዌብሳይት ችግሩ ምን እንደሆነ አንድ ጉዳዩን የሚያውቁ ባለሙያ ጥልቅ ማብራርያ ለሚድያችን ሰጥተዋል፣ ይከታተሉት
(መሠረት ሚድያ)- ዱባይ ላይ መቀመጫውን ባደረገው በቶፓን ሴኪዩሪቲ ሶሉሽንስ የበለፀገው አዲሱ የኢሚግሬሽን ሲስተም ስራ ጀምሯል ከተባለበት ጊዜ አንሰቶ እስካሁን ድረስ መጠነ ሰፊ ችግሮች እየተስተዋሉበት ይገኛል፡፡
ከቀድሞው የኢሚግሬሽን ድረ-ገጽ (ዌብሳይት) አንጻር የበፊቱ ላይ ያልነበሩ በአሁኑ በአዲሱ የአሰራር ስርዓት ላይ በተደጋጋሚ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች አሉ፡፡
ከእነዚህ ችግሮች ውስጥ አንዱ የኢሚግሬሽን ክፍያ ለመፈፀም ያስቀመጠውን ቅደም ተከተል በመከተል ለአንድ የኤሌክትሮኒክ ክፍያ (Electronic Payment) አንድ ጊዜ ብቻ ክፍያ መቀበል ሲገባው በሞባይል ባንኪንግ እና በቴሌ ብር የክፍያ አማራጮች ክፍያ በሚፈፅም ሰዐት በተዘረጋው የክፈያ ስርዐት ክፍያው መግባት አለመግባቱን በማጣራት ቶሎ አይለቅም።
እንዲሁም በአንድ የትእዛዝ ቁጥር (Order Code) ክፍያ ከተፈፀመ በኋላ በተደጋጋሚ 2 እና 3 ጊዜ ከዛም በላይ በእንድ የትዛዝ ቁጥር ክፍያ ከአንድ ሰው ሊቀበል ይችላል፡፡
ይህ ችግር ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ እንዲሁም ሲስተሙ በማይሰራና በተጨናነቀ ሰዓት ላይ በሞባይል ባንኪንግ በሚፈጸሙ ክፍያዎች መተላለፍ አለመተላለፉን ሲስተሙ ስለማያነብ ህበረተሰቡን ለተጨማሪ ኪሳራና እንግልት እየዳረገ ይገኛል፡፡
በአንድ የኤሌክትሮኒክ ክፍያ 2 እና 3 ጊዜ በተደጋጋሚ ሲስተሙ ክፈያ መቀበሉ ዝም ተብሎ እንደ ቀላል የሚታይ ጉዳይ አይደለም፡፡
በአዲሱ ሲስተም ላይ ባቀረቧቸው የክፍያ አማራጮች ላይ ይበልጥ ይህ ችግር ጎልቶ እየታየ ያለው የጠፋ ፓስፓርት፣ የፓስፖርት እድሳት፣ የስም እና እድሜ ማስተካከያ፣ የፈጣን ፓስፓርት የሚያወጡ ደንበኞች ላይ ነው፡፡
በተጨማሪም አገልግሎት ጊዜያቸውን ያልጨረሱ እና የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው ፓስፖርቶችን ሲስተሙ ለመለየት እንደተቸገረ ተስተውሏል፡፡
በዚህም ምክንያት ኢሚግሬሽን ሊሰጣቸው ከሚገቡ አገልግሎቶች ውስጥ የእድሳት፣ የስም እና እድሜ ማስተካከያ፣ የጠፋ ፓስፓርት እንዲሁም የመደበኛ ፓስፖርት አገልግሎት ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ ቆይቷል፡፡
ሌላው እየተስተዋለ ያለው ችግር ቅጣት የማይጣልባቸው ፓስፖርቶች ላይ ማለትም የአገልግሎት ጊዜያቸውን ያልጨረሱ እና የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ፓስፖርቶች በውል ሲስተሙ ለይቶ ባለማወቁ ምክንያት በአነስተኛ ከ8,000 ብር ጀምሮ አላስፈላጊ የሆኑ ካስቀመጡት መመሪያ ውጭ ቅጣት ማህበረሰቡ ላይ እየተጣለ ነው፡፡
በተለይም የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው ፓስፖርቶች ላይ የስም እና እድሜ ማስተካከያ እንዲሁም ለእድሳት የሚመጡ ደንበኞች ላይ ይህን ቅጣት ያለአግባብ ከህግ እና ከመመሪያው ውጭ የገንዘብ ቅጣቱን ይጥላል፡፡
እንደዚህ አይነት ችግሮች በአንድ የትዛዝ ቁጥር (Order Code) በተደጋጋሚ የሚፈፀም ክፍያና ከመመሪያው ውጭ የሆኑ ቅጣቶች የቀድሞ የኢሚግሬሽን ድረ-ገጽ ላይ የሌለ ሲሆን በአሁኑ አዲስ በዘረጉት ስርዓት ላይ በተደጋጋሚ እየታየ ይገኛል።
ማህበረሰቡ ኢሚግሬሽን ባስቀመጠው የክፍያ አማራጭ ተጠቅሞ ክፍያ ከፈጸመ በኋላ ክፍያው መግባት አለመግባቱን ሲስተሙ በአግባቡ ባለማንበቡ ምክንያት በአንድ ኮድ ተደጋጋሚ ክፍያ ስለሚቀበል አላስፈላጊ የሆነ ኪሳራ እያደረሰ ነው።
በተጨማሪም የተባለውን ክፍያ በአግባቡ ማስገባታቸውን ለማሳየት ክፍያውን የፈፀሙበትን የባንክ ስቴትመንትና የባንክ ሪሲት ይዘው እየሄዱ ለፈጣን አገልግሎት ከ2 ቀን እስከ 5 ቀን እናጨርሳለን ብለው በማስተወቂያ ያስነገሩትን ፓስፖርት ቀርቶ ጭራሽ አገልግሎት ሳያገኙ ያስገቡት ክፍያው መግባት አለመግባቱን ድርጅቱ እስኪያጣራ ድረስ ለሳምንታት ብሎም ለወራት በመመላስ እየተጉላሉ እንደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ።
ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች እንዳሉ ሆነው አንድ ደንበኛ በኢሚግሬሽን ቢሮ ውስጥ በሚስተናገድበት ወቅት እና በኦንላይን በሚሞላበት ወቅት በተደጋጋሚ የሚያጋጥሙ የሰርቨር መቆራረጦች ምክንያት የአንድ አመልካች ማመልከቻ ተሞልቶ እስኪያልቅ አንደማያስጨርስ ለመመልከት ችለናል፡፡
እየተስተዋሉ ካሉ ችግሮች ውስጥ ሌላው ሲስተሙ የተወሰነ መረጋጋት ኖሮ በሚሰራበት ሰዓት እንኳን የኢሜይል ኦቲፒ OTP (One-Time Password) በስርዓትና በተሳለጠ መልኩ በሰዓቱ አይልክም ፡፡
እንደ Microsoft ያሉ ግዙፍ አለማቀፍ ኩባንያዎች ተቀባይነት ያገኙት እንደ Windwos እና MicroSoft Office ምርታቾቻቸው በተጠቃሚ ዘንድ ያለው ቀላልነት (ease of user interface) እና የተደራሽነት ቅንብሮች ውስጥ ባሉ ባህሪያት በቀላሉ ለመጠቀም ምቹ መሆናቸው እንዲሁም ተጠቃሚዎች እይታዎችን እና የመተግበሪያ ዘዴዎችን በቀላሉ እንዲያስተካክሉና እንዲጠቀሙ ማስቻሉ ነው፡፡
አዲሱ የኢሚግሬሽን ዌብሳይት በተቃራኒው እጅግ የተወሳሰበና ከደንበኞች ፍላጎትና ለተጠቃሚዎች በቀላሉ ከመስራትና አገልግሎት ከመስጠት ይልቅ ትኩረቱ የሳይበር ደህንነት (cybersecurity) ላይ ያተኮረ በመሆኑ ምክንያት የአንድ የደንበኛ ፎርም ለመሙላት ቀለል መደረግ ሲገባው አላስፈላጊ የሆነ ቁም ስቅል ውስት በመክተት ላይ ይገኛል፡፡
ሌላ የታዘብነው አንድ የኢሚግሬሽን ፎርም በአዲቱ ዌብሳይት ለመሙላት ፎርም ከሰጠ በኋላ አንድ በማንኛውም ቢሮ ውስጥ የሚገኝ ዴስክቶፕ ኮምፒውተርን አቅም የሚፈትንም ሆኖ ተገኝቷል፡፡
አንድ ተራ የማመልከቻ ፎርም ለሙላት በአንድ ኮምፒውተር ላይ የሚያደርሰው ጫና የኮምፒውተሩን ሙሉ አቅም የሚጠቀም ሲሆን ሲፒዩ (CPU) እና የአየር ማራገቢያ (Fan) ከፍተኛ የሆነ ድምጽ እስኪያሰሙ ድረስ ጫናን ያደርሳል፡፡
ይህን ድረ-ገፅ ዲዛይን ያደረገው ድርጀት ከድረ-ገፅ ግንባታ ይልቅ የሳይበር ደህንነት (cybersecurity) ላይ ትኩረት አርጎ የሚሰራ ሲሆን ለተጠቃሚዎች ያስቀመጣቸው መመሪያዎችና መተግበሪያዎች በቀላሉ ምቹ ሳይሆኑ ቀርተው እና የአፈጻጸምና የክፍያ ስርዓቱ ላይ ችግሮችን እንደፈጠረ ተስተውሏል።
ድርጅቱ ለህብረተሰቡ በዌብሳይቱ ላይ ያሉ ግልጽ ያልሆኑ መመሪያዎች እና ግብረ መልሶች እንዲሁም አንድ ክፍያ ከተፈፀመ በኋላ መግባት አለማግባቱን የሚያረጋግጥበት ሂደት አስቸጋሪ ስለሆነ በአፋጣኝ ማስተካከያ እርምጃ ማድረግ ይገባል፡፡
***መሠረት ሚድያ ላይ የሚቀርቡ አስተያየቶች በሙሉ የፀሀፊዎቹ እንጂ የሚድያው አቋም እንዳልሆኑ ልናስታውስ እንወዳለን።
-መሠረት ሚድያ-





የማፍያዎቹ መስሪያቤት ኢምግሬሽናችን
The technology they are using is just shit. Flutter web new yetetekemut for the new system and its not recommended for such systems. The load time is insane plus frequent disconnect to the server. I have no idea who in their right mind thought this would be a good idea.