Discussion about this post

User's avatar
kassahun Endeshaw Engedaw's avatar

ወዳጄ በፃፉት ሀሣብ እንደ ሀሣብ እስማማለሁ በአንድ ጀምበር እማ የሚለወጥ ነገር የለም! በትግልም አመት እና ምዕተ አመታትንም የሚወስዱ ፅናትን የሚጠይቁ ጉዳዮች አሉ።ለምሣሌ የሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ ከድህነት ለመውጣት የሚደረግ ግላዊ እና ሀገራዊ ልፋት በተለይ ከተስፋ ጋር በህብረት ሲሆን ብዙ መስዋትነት እየተከፈለም ልክ እንደቻይናውያኑ፣ እንደ ጃፓናውያኑ ቁርጥ የለ የመለወጥ ህዝባቸውን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ማንነታቸውን አሣልፈው የሠጡ መሪዎች ባሉበት እርሶም ባነሡዋት አሜሪካ ጭምር መራር የሆኑ ሂደቶችን አይተናል። ነገር ግን ወዳጄ እንደኢትዮጵያ ባሉ እንደኔይቱ ሀገሮች እንደዚህ አይነቱ ተስፋ ያለ አይመስለኝም። በተለይ የግል ስበዕነቸውን እና ምቾታቸውን ብቻ ለመገንባት የሚጥሩ መሪዎች ፣በራሳቸው ጭንቅላት ሣይሆን በጥቅም ፈላጊ አጋር መሣይ ጠላቶች ሀገራቸውን የሚመሩ ፣ የሩቅ ጊዜ ብሔራዊ እቅድ የሌላቸው፣ ሀገሪቱን አንድ ወደፊት ያስኬዱ መስለው ሁለት ሶስት ጊዜ ወደኋላ የሚጎትቱ፣ የአስተሣሠብ ነቀርሳ የመረዛቸው መሪዎች በሚይዟት እና በሚመሯት ሀገር ግን አስቸጋሪ እንደሚሆን ነው። መርጠን እናውቃለን በመሠለን እርሶም እንዳሉት -97ቱም _2014ቱም ከዚያ በፊት በነበሩትም በትግል ጉዞው የራስን አስተዋፅዖ ለማበርከት ፡የዘንድሮው ግን እኮ ምርጫ የሚባል ሳይንስ ውስጥ የሚገባ ሂደት አይደለም። የአንድ ክፍል ተማሪዎች አለቃቸውን ለመምረጥ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እና የተፎካካሪዎች ግብ ግብ የመራጮች እጅን የማውለብለብ ነፃነትን ያህል የማይሆን ኩነት ነው። አእንደውም የሀገርን ሀብት በይስሙላ እንደማባከን ነው የመሠለኝ። ለታይታ! ማንን ለመምረጥ ልሳተፍ !? ምን አይቼ ድምፄን ለመን ልስጥ ገና ለገና ዲሞክራሲ ሂደት ነው ብዬ የማላውቀውን ድጋፌን ልቸረው? ግራ ገብቶን እኮ ነው? ወይስ እንደልጆች ጨዋታ “አሌ ቡም” ብዬ በጄ ጣቶች ቁጥር ሰጥቼ ባቦሠጡኝ ልመርጥ ነው? የማላውቀውም መለዓክ የማውቀውም ሠይጣን ለኔ ያው ናቸው! ስለዚህ ወዳጄ ሆይ እኔ በዚህ ምርጫ የመረጥኩት ድምፀ ተአቅቦን ነው! ይህም የዲሞክራሲው እድገት አንዱ ማሣያ በመሆኑ!

No posts

Ready for more?