አዲስ አበባ ውስጥ ሽብር ለመፍጠር ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ አስር ተከሳሾች እስከ ሞት ሊያስቀጣ በሚችል የሕግ አንቀፅ እንዲከላከሉ ፍርድ ቤት ዛሬ ብያኔ ሰጠ
(መሠረት ሚድያ)- የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የሕገ-መንግሥት እና የፀረ-ሽብር ወንጀል ምድብ በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት ሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ከናሁሰናይ አንዳርጌ ጋር በመሆን በአዲስ አበባ የሽብር ወንጀል ሊፈፅሙ ነበር የተባሉ አስር ግለሰቦች ላይ ብይን ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ዓቃቤ ሕግ ክሱን በምስክር እና በማስረጃ በማረጋገጡ ልትከላከሉ ይገባል ብሏል።
ድርጊቱ ተፈፀመ ከተባለ ከሁለት ዓመት በኋላ በዛሬው ዕለት ሰለሞን ፍቃዴ፣ አሸናፊ ይሁነው፣ ገብረማሪያም ሰጠኝ፣ አማኑኤል ያለው እና በአጠቃላይ አስር ተከሳሾች የዓቃቤ ሕግን ምስክር እና ማስረጃ በበቂ ሁኔታ መከላከል ካልቻሉ የእድሜ ልክ ከዚያም ከፍ ሲል የሞት ቅጣት ሊጠብቃቸው እንደሚችል ፍርድ ቤቱ ዛሬ በይኗል።
ተከሳሾቹ ለሁለት ዓመታት ያህል ዋስትና መብት ተከልክለው በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንደሚገኙ የመሠረት ሚዲያ ምንጮች ጠቁመዋል።
ድርጊቱ ተፈፀመ በተባለበት ወቅት በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተለይ ወጣቶች በፀጥታ ግብረ ኃይል ታፍሰው በአዲስ አበባ እና በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤቶች ለወራት ያህል ታስረው መቆየታቸው ይታወሳል።
-መሠረት ሚድያ-




ይህም ፓርቲ ይህም ጊዜ ያልፋል
ትዝብቱ ለታሪክ ይቀመጣል