ወጣቱ የት ገባ? የዛሬ አመት ቦሌ ራካን ህንፃ አካባቢ ደብዛው የጠፋው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ጉዳይ
(መሠረት ሚድያ)- የሶስት ልጆች አባት የሆነው አደራጀው የሺዋስ (ኤዲ) ለመጨረሻ ከቤተሰቡ ጋር የተገናኛው የዛሬ አመት ገደማ ህዳር 8/2017 ዓ.ም ጠዋት ላይ ነበር።
በወቅቱ ዜጋ ከሆነባት አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ አንድ አመት ሞልቶት የነበረው ግለሰቡ ጠዋት ላይ ከቤተሰቡ ጋር ንግግር አድርጎ እንደነበር፣ ከሰአትም ከሰው ጋር ሊገናኝ ቀጠሮ ይዞ እንደነበር ቤተሰቦቹ ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።
ከዛ ግን ደሳለኝ ሆቴል የቀጠረውን ሰው ለማግኘት እንደወጣ በዛው ደብዛው ጠፍቶ እንደቀረ ታውቋል።
"እኛ በራሳችን መንገድ ከመፈለግ ባሻገር ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ማለትም ለአዲስ አበባ ፖሊስ እና ለፌዴራል ፖሊስ ያሳወቅን ሲሆን በፌዴራል ፖሊስ የጠፉ ሰዎች ማፈላለጊያ መተግበሪያ (App) ላይ እንዲመዘገብና እንዲለጠፍ አድርገናል" የሚሉት ቤተሰቦቹ አሁን ላይ ጉዳዩ አመት በማለፉ ወደ ሚድያ ለማውጣት እንደፈለጉ ያስረዳሉ።
የወጣት አደራጀውን ጉዳይ ለአሜሪካን ኤምባሲ በአካል እና በስልክ ማመልከታቸው የታወቀ ሲሆን እስካሁን ድረስ ግን ምንም አይነት ፍንጭ ሊያገኙ አለመቻላቸው ታውቋል።
"ኤዲ ከማንም ጋር ፀብ አልነበረውም፣ የምንጠረጥረው ሰውም የለም። በእለቱ ከቤቱ እንደወጣ በዛው ቀርቷል" የሚሉት ቤተሰቦች ከፍተኛ ጭንቅ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ወጣቱ ያለበትን የሚያውቅ በዚህ ስልክ ቤተሰብ ማግኘት ይችላል: +251920256451
-መሠረት ሚድያ-




ኢትዮጵያ ላለነው አላሰባችሁልንም
በምን ከፍለን ሙሉ አገልግሎቱን እናግኝ??🤔