#Announcement ከመሠረት ሚድያ መስራች ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት የተላለፈ መልዕክት
ለውድ የመሠረት ሚዲያ ተከታታዮች፣
መሠረት ሚዲያን ከአንድ አመት ተኩል በፊት በመጀመር እና ከእናንተ ጋር አብረን በመገንባት ያሳለፍነው ጉዞ በሙያዬ ውስጥ ከሚታወሱ ተሞክሮዎቼ አንዱ ነው። በእናንተ ድጋፍ መሠረት ሚዲያ በአጭር ጊዜ ውስጥ በፍጥነት በማደግ በርካታ ዜናዎችን አቅርቦ ለብዙ አንባቢዎች መድረስ ችሏል።
አሁን ግን አሜሪካን ሀገር ውስጥ ባለ አንድ የሚዲያ ተቋም ውስጥ የሙሉ ሰዓት (full time) የስራ ምዕራፍ ልጀምር እንደሆነ ለእናንተ ማጋራት ፈለግሁ፣ መሠረት ሚዲያ ግን ሥራውን አጠናክሮ ይቀጥላል።
ይህ መድረክ ተሞክሮ ባላቸው ጋዜጠኞች በመመራት የእውነተኛና ነጻ ጋዜጠኝነት ተልዕኮውን በመቀጠል የህዝብ ድምፅ ሆኖ ይሰራል፣ እኔም በቦርድ አባልነት ለተወሰነ ግዜ እቀጥላለሁ። ለመሠረት ሚዲያ ላሳያችሁት ድጋፍ፣ እምነት እና ተሳትፎ በጣም እጅግ አመሰግናለሁ።
መሠረት ሚዲያን መከታተልና መደገፍ ቀጥሉ: https://meseretmedia.substack.com/30pcoff
ከአክብሮት ጋር፣
ኤልያስ መሠረት




congratulations
Life time best Journalist Mese Tysm.