የኢትዮጵያ አየር መንገድ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ ስድስት ኤርባስ A350 አውሮፕላኖችን ለመግዛት በዱባይ የአየር ትርዒት ላይ ውል አሰረ
(መሠረት ሚድያ)- የአፍሪካ ግዙፉ የአየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስድስት ኤርባስ A350 አውሮፕላኖችን ማዘዙን አውሮፕላን አምራቹ ከደቂቃዎች በፊት አስታውቋል።
ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን ከአፍሪካ ትልቁ የA350 ባለቤት የሚያደርገው ሲሆን ምቹ እና ነዳጅ ቆጣቢ በረራዎችን ለማድረግ እንደሚያግዘው ኤርባስ ጠቁሟል።
አየር መንገዱ አውሮፕላኖቹን እንደሚገዛ ይፋ የሆነው እየተካሄደ ባለው የዱባይ የአየር ትርዒት (Air Show) ላይ ሲሆን ተጨማሪ 11 ቦይግን 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ከቦይንግ ኩባንያ ለመግዛት መዋዋሉ ትናንት ይፋ ተደርጎ ነበር።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁን ላይ 22 ኤርባስ ኤ350 አውሮፕላኖች አሉት። አየር መንገዱ ኤ350 አውሮፕላኖች በዓለም ዙሪያ ለሚያጓጉዛቸው መንገደኞቹ እጅግ ዘመናዊ፣ የላቀ እና ምቹ አገልግሎትን ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብሏል።
-መሠረት-



