የአቢሲንያ ባንክ ደንበኞች ወደ ሌሎች ባንኮች የሚልኩት ገንዘብ ከአካውንታቸው ተቀናሽ ቢሆንም ገንዘቡ ለተቀባይ እየደረሰ አለመሆኑን ተናገሩ
(መሠረት ሚድያ)- በቅርብ ቀናት በርከት ያሉ የአቢሲንያ ባንክ ደንበኞች ቅሬታቸውን ለመሠረት ሚድያ በፅሁፍ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፣ ይህም ከባንኩ አካውንት ወደ ሌላ ባንኮች ከሚላክ ገንዘብ ጋር የተገናኘ ነው።
የባንኩ ደንበኞች እንደሚሉት ባንኩ ምንም አይነት መረጃ ለደንበኞቹ ሳይሰጥ ወደ ሌሎች ባንኮች የሚልኩት ገንዘብ ከአካውንታቸው ተቀናሽ ቢሆንም ገንዘቡ ለተቀባይ እየደረሰ አለመሆኑን ተናገረዋል።
ከህዳር 22/2018 ዓ.ም ጀምሮ የተከሰተው ይህ ችግር በርካቶችን ገንዘባቸው ተይዞባቸው እንዲቆይ እንደዳረጋቸው፣ በዚህም ስራ መስራት እና ገንዘብ መክፈል እንዳልቻሉ ይጠቅሳሉ።
"የባንኩ 'transfer to other banks' አገልግሎት በመያዙ ለከፋ ችግር ተዳርገናል" የሚሉት የባንኩ ተጠቃሚዎች በባንኩ የፌስቡክ ገፅ ጭምር አስተየየት መስጫ ላይ ችግራቸውን ቢፅፉም ምላሽ ማግኘት እንዳልቻሉ ያስረዳሉ።
"የዲጂታል ቡድኑ ወይም የባንኩ አመራሮች የተከሰተውን ችግር አሳውቀው እና ይቅርታ ጠይቀው ማስተካከል ሲኖርባቸው ዝም ብለዋል፣ ይህም ችግሩን አቃሎ ማየት እና ደንበኞችን አለማረዳት ነው የሚል ግምት እንድንወስድ አድርጎናል" በማለት አንድ ስሜ አይጠቀስ ያሉ ደንበኛ ተናግረዋል።
"የህዝብን ገንዘብ ለበርካታ ቀናት አግቶ ይዞ መቆየት ምን ማለት ነው? ለምን ግልፅ መረጃ አይሰጡም? ብዙ ሰው ንግድ ተበላሽቶበታል፣ የትምህርት ቤት ክፍያ እንኳን መክፈል ያልቻሉ አሉ" የሚሉት ሌላኛዋ የባንክ ደንበኛ ናቸው።
መሠረት ሚድያ በዚህ ዙርያ አቢሲንያ ባንክን መረጃ ጠይቋል።
ከሰሞኑ ወደ ሌሎች ባንኮች የሚደረጉ የገንዘብ ችግሮች መከሰታቸውን በማረጋገጥ የጀመረው የባንኩ ምላሽ ችግሩ በግዜያዊ የቴክኒክ መቆራረጥ መሆኑን ይጠቅሳል።
"ችግሩ የተፈጠረው በባንኩ 'external interbank settlement ecosystem' ውስጥ ነው። እንደተባለው ከላኪዎች ላይ ገንዘብ ቢቆርጥም የማረጋገጫ እና ክፍያ የመፈፀም ሂደቱ መዘግየት አጋጥሞታል። በዚህ አጋጣሚ ችግሩ የደህንነት መጣስ አለመሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፣ ከደንበኞቻችን ገንዘብ ውስጥም የጠፋ የለም" ብሏል።
ባንኩ ምን ያህል ደንበኞች በዚህ ችግር እንደተጠቁ ከመግለፅ የተቆጠበ ሲሆን አሁን ላይ እያንዳንዱን መዘግየት ያጋጠመውን የገንዘብ ትራንስፈር የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።
"ለደንበኞች መረጃ ባለመስጠት ዙርያ ያለውን ሁኔታ እንረዳለን። ባንኩ መረጃ ከመስጠቱ በፊት የቴክኒክ ዳሰሳ በማድረግ ትክክለኛ መረጃ ለመስጠት ከማሰብ የመነጨ ነው" በማለት አሁን ላይ ኦፊሴላዊ መግለጫ እየተዘጋጀ መሆኑን አንስቷል።
በመጨረሻም ደምበኞች 'በአጭር ግዜ' ገንዘባቸው እንደሚስተካከል ገልፆ ለተፈጠረው ሁኔታ መፀፀቱን ገልጿል።
-መሠረት ሚድያ-





Thank you Meseret Media for bringing this issue to light. The banking sector has many deep rooted problem too often operating as if their only responsibility is to shareholders, not customers. The situation with Bank of Abyssinia shows this clearly: people’s money has been stuck for nearly two weeks with no proper communication or accountability.
What makes it worse is that even the National Bank’s consumer protection system is failing the people as well: the complaint email they put on the website is invalid(complaintoffice@nbe.gov.et) , and there is no clear channel for customers to seek help. How can the public trust the system when neither the banks nor the regulator communicate transparently?
Before forcing people to put their hard earned money into banks, the system should be reliable, transparent, and accountable. Customers should never be left helpless when their own money is withheld for weeks.
This column was necessary, and I appreciate Meseret Media for giving customers a voice when official institutions have not.
Subject: Feedback on Recent Banking App Issue
Dear Team Meseret,
I am an avid reader of your column and wanted to share my perspective on a recent issue.
Based on my experience, this problem is not limited to a single bank—it appears to be affecting banks across the board. In fact, some have even removed the CBE application from their list. I’ve encountered the same issue with another private bank that I use.
For this reason, attributing the issue to one specific bank may not be entirely fair. I humbly suggest looking further into the matter by checking with other banks, and if possible, with the ET Switch system, to identify the root cause.
Thank you for your attention to this matter.
Best regards,
Yonas G