የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጥያቄ ያስነሳበትን የቫት ክፍያ በሚመለከት ማብራርያ ሰጠ
(መሠረት ሚድያ)- ሚድያችን ከሁለት ቀን በፊት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከመስከረም ጀምሮ ያለ ውዝፍ የቫት ክፍያ በአስገዳጅነት ማስከፈል መጀመሩን መዘገቡ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎም ከሰሞኑ በርካቶች የኤሌክትሪክ ክፍያ ሲሞሉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ተቆርጦባቸው በምትኩ የሚሞላላቸው ገንዘብ አነስተኛ መጠን ብቻ እንደሆነ ሲናገሩ ነበር።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚድያችን ዘገባን ተከትሎ በዛሬው እለት የቫት ክፍያን በተመለከተ ማብራርያ መስጠቱን ተመልክተናል።
"አንድ የመኖሪያ ቤት ደንበኛ ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ሲከፍል የአገልግሎት ክፍያ፣ የተቆጣጣሪ ባለስልጣን ቀረጥ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ለኢቲቪ የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ እና የአገልግሎት ክፍያ ተጨማሪ እሴት ታክስ አብሮ ይይዛል" የሚለው ተቋሙ አሠራሩ ደንበኞች በወር ውስጥ የተጠቀሙት የኃይል ፍጆታ ሲባዛ ወቅታዊ የአንድ ኪዋሰ ታሪፍ ማባዣ እና ከላይ የተዘረዘሩትን ክፍያዎችን የሚያጠቃልል ይሆናል ብሏል።
"ለምሳሌ በዚህ በሐምሌ ወር ከ301 እስከ 400 ኪዋሰ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም አንድ 'የድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኛ' የአንድ ኪዋሰ ወቅታዊ የታሪፍ ማባዣ መጠን 4.4898 ብር ነው" በማለት ስሌቱን በዚህ መልኩ አቅርቧል።
"በዚህ መሰረት ደንበኛ በሐምሌ ወር ውስጥ 350 ኪዋሰ ተጠቅመዋል ብለን ብናስብ፡-
☑️ ወርሃዊ የኃይል ፍጆታ ▶️ 350 ኪ.ዋ.ሰ*4.4898 ብር (ወቅታዊ የታሪፍ ማባዣ) 🟰 1,571.43 ብር፣
☑️ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ክፍያ ▶️ (ወርሃዊ የኃይል ፍጆታ በኪዋሰ*15%) ፤ ይህ ማለት 1,571.43*15% 🟰 235.7145 ብር፣
☑️ የአገልግሎት ክፍያ /ከ50 ኪ.ዋ.ሰ በላይ ፍጆታ ለሚጠቀሙ ደንበኞች/ 🟰 46.75 ብር፣
☑️ የአገልግሎት ክፍያ ተጨማሪ እሴት ታክስ ▶️ የአገልግሎት ክፍያ*15% ይህም ማለት 46.75 ብር *15% 🟰 7.0125 ብር፣
5. ለተቆጣጣሪ ባለስልጣን የሚከፈል ቀረጥ/ ▶️ (ወርሃዊ የኃይል ፍጆታ በኪዋሰ+የአገልግሎት ክፍያ)*0.5% ይህም ማለት (1,571.43 + 46.75)*0.5% 🟰 8.0909 ብር፣
6. ከ50 ኪ.ዋ.ሰ በላይ ለኢትጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን (ኢቲቪ) የሚከፈል 🟰 10 ብር፣
በመሆኑም ከላይ በተቀመጠው አሠራር መሰረት የደንበኛው ወርሃዊ የኤሌክሪክ ፍጆታ ሂሳብ እንደሚከተለው ይሆናል፡
➡️ ወርሃዊ ፍጆታ (1571.43 ብር)
➡️ የተጨማሪ እሴት ታክስ (235.7145 ብር)
➡️ የአገልግሎት ክፍያ (46.75 ብር)
➡️ የአገልግሎት ክፍያ ተጨማሪ እሴት ታክስ (7.0125 ብር)
➡️ የተቆጣጣሪ ባለስልጣን የሚከፈል (8.0909 ብር)
➡️ ለኢቲቪ የሚከፈል የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ (10 ብር) ✅ ጠቅላላ ድምር 🟰1,878.9979 ብር (1 ሺህ 878 ብር 9979 ሳንቲም) ደንበኛው ይፈፅማል።
የኤሌክትሪክ እና የውሃ አገልግሎት በገደብ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እንዲከፈልባቸው የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የዛሬ አመት ገደማ ነበር።
አዲሱ አዋጅ ለሁለት አስርት ዓመታት በስራ ላይ ቆየውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ እና ከዛ በኋላ እሱን ለማሻሻል ሁለት ጊዜ የወጡትን የማሻሻያ አዋጆች ሙሉ በሙሉ የሚሽር ነው።
“አነስተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ያለበትን ወጪ ለማርገብ ሲባል” የኤሌክትሪክ እና የውሃ አገልግሎት ከታክሱ ነጻ ተደርገው እንደነበር አዋጁ ማብራሪያ ላይ ሰፍሯል። በስራ ላይ ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ከ20 ዓመት በፊት በ1994 ከወጣ በኋላ ለሁለት ጊዜያት ያህል ማሻሻያ ተደርጎበታል።
መረጃን ከመሠረት!



