አቶ ኤርሚያስ አመልጋን ጨምሮ ህገወጥ የገንዘብ ማሰባሰብ ላይ በመሳተፍ የተጠረጠሩ ላይ ምርመራ መጀመሩ ተሰማ
(መሠረት ሚድያ)- የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አቶ ኤርሚያስ አመልጋን እና "ጀነሲስ ኢንቨስትመንት ሰርቪስ" የተባለ ኩባንያን ህገወጥ በሆነ መንገድ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮችን ለህዝብ በመሸጥ ገንዘብ ሲያሰባስቡ በነበሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን ተቀብሎ ምርመራ መጀመሩ ተሰምቷል።
ባለስልጣኑ ያወጣውን መግለጫ ጠቅሶ ካፒታል እንደዘገበው በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ህገወጥ የሰነድ ሽያጭን በመጠቀም ከህዝብ ገንዘብ በማሰባሰብ ተግባር ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል።
በተለይም በአቶ ኤርሚያስ አመልጋ እና በ"ጀነሲስ ኢንቨስትመንት ሰርቪስ" ኩባንያ ላይ እየተካሄዱ ያሉት ምርመራዎች በህገ መንግስት የተረጋገጠ የመሰማት እና የመከላከል ሙሉ መብታቸው በተጠበቀ ሁኔታ እንደሚከናወኑ ባለስልጣኑ አረጋግጧል።
በተጨማሪም ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ከካፒታል ገበያ ጋር በተያያዙ እንቅስቃሴዎች ላይ ሲሳተፍ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።
በተለይም በንግድ ድርጅቶች ምስረታ ላይ ሲሳተፉ የንግድ ምዝገባ እና ምስረታ ሰነዶችን ከሚመለከተው አካል እንዲያረጋግጡ እንዲሁም ገንዘብ ከመክፈላቸው በፊት በባለስልጣኑ ፈቃድ ከተሰጣቸው የኢንቨስትመንት አማካሪዎች ብቻ ምክር እንዲፈልጉ ጠቁሟል።
ባለስልጣኑ ፈቃድ ሳይኖራቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት የሚሰጡ ወይም ለማቅረብ የሚሞክሩ አካላት ካሉ ለባለስልጣኑ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፣ በእንደዚህ አይነት ህገ-ወጥ ድርጊቶች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ አረጋግጧል።
Via Capital




አገዛዙ እኔ ብቻ ነኝ ገንዘብ ሰብስቤ የማዋቅራቹ እያለ ነው
Hi messy, i can't let us grow apart! I follow you wherever you go