በህንድ የሚገኙት የኢትዮጵያ አምባሳደር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ አነጋጋሪ ሆኗል
(መሠረት ሚድያ)- በህንድ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር በመሆን በቅርቡ የተሾሙት እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለበርካታ አመታት በዲፕሎማትነት ያገለገሉት አምባሳደር ፍሰሀ ሻውል ገብሬ ANI ከተባለ የህንድ ሚድያ ጋር ያደረጉት ቃለ መጠየቅ በብዙዎች ዘንድ አነጋጋሪ ሆኗል፣ የፓኪስታን መንግስትንም ሳያስቆጣ አልቀረም።
አምባሳደሩ ከአንድ ቀን በፊት በዚህ ቃለ መጠይቅ ላይ በቅርቡ በህንድ እና ፓኪስታን መሀል ተከስቶ በፍጥነት የበረደውን እና የ26 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈውን ግጭት በተመለከተ አስተያየት ሲሰጡ ፓኪስታንን ግጭቱ ተጠያቂ አድርገው ተናግረው ነበር።
መሠረት ሚድያ በተመለከተው እና በዚህ ሊንክ ላይ በሚገኘው ቪድዮ ላይ አምባሳደሩ በግልፅ ፓኪስታንን ለግጭቱ መነሳት ሲከሱ ይታያል: https://www.indiatoday.in/world/story/ethiopia-embassy-india-envoy-pakistan-remark-pahalgam-terror-attack-2727899-2025-05-21
"እኛ የሽብር ጥቃቱን አውግዘናል፣ ህንድ ሀላፊነት በተሞላበት ሁኔታ እርምጃ ወስዳለች። ችግር ለመፍጠር ወደ ፓኪስታን የሄዱት ህንዶች አይደሉም፣ ፓኪስታኖች ናቸው ችግር ለመፍጠር ወደ ህንድ የመጡት" ያሉት አምባሳደር ፍሰሀ ፓኪስታኖች ሰዎችን በማንነታቸው እየለዩ እንደነበር ገልፀው ይህም 'በጣም መጥፎ' ነው ብለው ገልፀውታል።
ይህን በዲፕሎማሲ አካሄድ 'አጠያያቂ' የተባለ ንግግር ተከትሎ በህንድ የሚገኘው እና ራሳቸው አምባሳደሩ የሚመሩት ሚስዮን ማብራርያ ሰጥቷል።
"የአምባሳደሩ ንግግር ከአውድ ውጪ ተወስዷል። ኤምባሲው የሽብር ተግባርን በመግለጫው ቢያወግዝም ከሁለቱም ሀገራት ጋር የተመጣጠነ ግንኙነት አላት" በማለት ጉዳዩን ለማለዘብ የሚመስል መግለጫ በኤምባሲው ተሰራጭቷል።
መረጃን ከመሠረት!




ያለመብሰል ክፋቱ.....
He is brilliant ambassador