አምነስቲ ኢንተናሽናል የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝደንት ከእስር እንዲፈታ ጠየቀ
(መሠረት ሚድያ)- የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝደንት ዶ/ር ዮናታን ዳኘው ከእስር እንዲፈታ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ማምሻውን ጠየቀ።
"መንግስት ሰላማዊ የመሰብሰብ መብትን ማክበር አለበት" ያለው አምነስቲ የጤና ባለሙያዎች ላይ የሚደርሰው መዋከብም እንዲቆም ጠይቋል።
በደሴ ቦሩ ሜዳ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች በዛሬው እለት እያሰሙት ከነበረው የመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የፀጥታ ሀይሎች ከስራቸው ላይ በማስነሳት ከነ ደንብ ልብሳቸው (ጋውናቸው) በመኪና ጭነው እንደወሰዷቸው ይታወሳል።
የጤና ባለሙያዎቹ ወደ 5ኛ ፖሊስ ጣብያ እንደተወሰዱ የታወቀ ሲሆን ከእስሩ በፊት "እየራበን እንድንሰራ አንገደድም" በሚል ግቢ ውስጥ ላማዊ የሆነ ሰልፍ አርገው ወደ ስራቸው እንደተመለሱ ታውቋል።
ይንና ወዲያው የፀጥታ አካላት በበርካታ ተሽከርካሪዎች ወደ ጤና ተቋሙ በመግባት ከ10 በላይ የጤና ባለሙያዎችን ይዘው እንደሄዱ ጉዳዩን ከሚከታተሉት ገፆች አንዱ 'Dr. Debol' ፅፎ ተመልክተናል።
ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ ዮናታን ዳኛው እንዲሁም ሦስት የአርባ ምንጭ ጠቅላላ ሆስፒታል ዶክተሮች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።
መረጃን ከመሠረት!




Justice not served in this nation.