ከአማራ ክልል የፀጥታ መደፍረስ ጋር በተገናኘ በሽብር ተጠርጥረው በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች በዛሬው ዕለት የርሀብ አድማ ማድረግ ጀመሩ
(መሠረት ሚድያ)- በአማራ ክልል የፀጥታ መደፍረስ ጋር በተገናኘ በሽብር ተጠርጥረው በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች የፌደራሉ መንግስት በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈፀመ ነው ያሉትን ግድያ፣ እስር እና ወከባ በፅኑ በመቃወም የርሀብ አድማ ማድረጋቸው ተሰምቷል።
የፖለቲካ እስረኞቹ ጠበቆች ለሚድያችን እንደተናገሩት በአዲስ አበባ በኮሪደር ልማት ስም በርካታ ዜጎች ተፈናቅለው ሜዳ ላይ በፈሰሱበት፣ የከተማዋ ወጣቶቾ በሕገ- ወጥ መንገድ ታፍሰው የት እንደገቡ ባልታወቀበት፣ ከሦስት መቶ በላይ የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ፍትሕ በእስር ቤት ታጉረው በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት "አዲስ ዓመት ገና አልጠባም" በሚል ከዛሬ ጷግሜ አምስት የአዲስ ዓመት ዋዜማ ጀምሮ በርሀብ አድማ ላይ ይገኛሉ።
በቂሊንጦ፣ በቃሊቲ፣ በአባ ሳሙኤል፣ በዝዋይ፣ በአዲስ አበባ እና በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤቶች ከሦስት መቶ በላይ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ከአማራ ክልል የፀጥታ መደፍረስ ጋር በተገናኘ ታስረው ይገኛሉ ሲሉ ጠበቆቻቸው ለመሠረት ሚዲያ ተናግረዋል።
በወቅቱ የተፋጠነ ፍትሕ ባለማገኘቱ ምክንያት የሁለት እስረኛ ቤተሰቦች ራሳቸውን ማጥፋታቸውን እና ቤተሰቦቻቸው ወደ ጎዳና መውጣታቸውን በያዝነው ሳምንት መዘገባችን ይታወሳል።
-መሠረት ሚድያ-


