(መሠረት ሚድያ)- በእስር ላይ የሚገኙ 28 የአማራ ፖለቲከኞች፣ ምሁራንና ጋዜጠኞች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው መሆኑንና ከእነዚህም መካከል ስምንቱ ከባለፈው ቅዳሜ ወዲህ ወደ ቅጣት ክፍል ተዛውረው በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ተናገሩ።
በኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ የሚመራው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ያቀረበውን ቅድመ ሁኔታ አንፈርምም በማለታቸው ምክንያት ሳይፈቱ የቀሩት አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣ መስከረም አበራ፣ ዳዊት በጋሻው፣ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ እና ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያምን ጨምሮ 28 እስረኞች ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገው እንደሚገኙ ተሰምቷል።
ከቤተሰቦች እና ከማረሚያ ቤት ምንጮች እንደሰማነው ከነበረበት አስከፊ እስር ቤት ወደ ተሻለ ቦታ ተዛውሮ የነበረውን ዶ/ር ወንደሰን አሰፋን ጨምሮ ስምንት ታሳሪዎች ድንገተኛ የቦታ ዝውውር ተደርጎባቸዋል። በዚህም መሠረት፡-
• ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ
• አቶዮሐንስ ቧያለው
• ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው
• እስክንድር ሽፈራው
• ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው
• ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም
• መለሰ ቸሩ እና
• መንበር አለሙ ህዳር 12/2019 ዓ/ም ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ድንገት ከቂሊንጦ እና ከቃሊቲ ማረሚያ ቤቶች እንዲወጡ ተደርገው የቅጣት እስር ቤት ተብሎ ወደሚታወቀውና በተለምዶ 'ታንከር' ወደሚባለው ክፍል መግባታቸውን ቤተሰቦቹ አስታውቀዋል።
በዚህም የተነሳ ስምንቱም ታሳሪዎች በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ የጤና እክልና ህመም ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል። ከእነዚህ ስምንት ታሳሪዎች መካከል አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ መንበር አለሙ እና እስክንድር ሽፈራው ቀደም ሲል ከዚሁ 'ታንከር' ከተባለ የቅጣት ቦታ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲወጡ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም በድጋሚ ተመልሰው እንዲገቡ መደረጋቸውን ምንጮች አመልክተዋል።
"ይህ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተገዢ አለመሆኑን የሚያሳይ ከመሆኑም ባሻገር ፍርድ ቤቶችም ለሚቀርቡላቸው አቤቱታዎች አፋጣኝ መፍትሄ አለመስጠታቸው በአስፈጻሚው አካል ተጽዕኖ ሥር መውደቃቸውንና በሀገሪቱ የሰብዓዊ መብት አያያዝ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ያመለክታል" በማለት የአንድ ታሳሪ ቤተሰብ ለሚድያችን ተናግረዋል።
አክለውም "በሀገር ውስጥ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በአማራ የፖለቲካ እስረኞች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል እንዲያወግዙ እንጠይቃለን። በተለይም በኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ የሚመራው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከማረሚያ ቤቱ ጋር በመተባበር እየፈጸመው ነው ያሉትን ግፍና ስቃይ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲያሳውቁ እንጠይቃለን" ብለዋል።
| መሠረት ሚድያ |




የአብይን ገዳይ አፋኝ ገራፊ
አገዛዝ እንደ ህወሃት
ፊት ለፊት ወቶ መፋለም ተገቢ ነው
ይሄ ገዳይ አካይስት ሰውዬ ከዚህ
በላይ ኢትዮጵያ ምድር ላይ በቆየት የለበትም