የኦሮሚያ ክልል መደበኛ እና የአድማ ብተና ፖሊስ ሰራዊት በአዲስ አበባ ውስጥ የሚሰማሩበትን ሕግ ምክር ቤቱ አጸደቀ
(መሠረት ሚድያ)- በዛሬው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው አዲሱ የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ በምክር ቤት አባላት ዘንድ አከራካሪ ሆኖ ፀድቋል።
በሕጉ ውስጥ የተካተተው አከራካሪው አንቀፅ 25 ንዑስ አንቀጽ 3 ሲሆን “የኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለው የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ተቋማት፣ ንብረቶች፣ ገንዘብ እና ሰነዶች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች የማየት ስልጣን አላቸው” የሚለው ነው።
ይህንን ለማስፈፀም ደግሞ የክልሉ መደበኛ ፖሊስ እና አድማ ብተና ፖሊስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሊሰማራ መሆኑንም የመሠረት ሚዲያ ምንጮች ጠቁመዋል።
ይህ የሥነ-ሥርዓት ሕግ በ2013 ዓ/ም ጀምሮ በተደጋጋሚ ለፓርላማው እየቀረበ ተቃውሞ ሲያስተናግድ ቆይቷል።
አምስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህንን ሕግ ለማጽደቅ ተስኖት የቆየ ሲሆን አሁን የስራ ዘመኑ ሊጠናቀቅ ሦስት ወራት ብቻ የቀረው ስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያጸድቀው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካይ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) እና አቶ አበባው ደሳለኝ ከረር ያለ ተቃውሞ አንስተው ተሟግተዋል።
ይሁን እንጂ ይሄው የሥነ-ሥርዓት ሕግ በአብላጫ ድምፅ መጸደቁን ለመሠረት ሚዲያ የደረሱት መረጃዎች ያሳያሉ።
-መሠረት ሚድያ-


