መንግስት አዲስ የነዳጅ ማደያ እንዳይከፈት ቢያግድም በውስጥ ስምምነት ለመክፈት እስከ 10 ሚልዮን ብር ጉቦ እየተጠየቀ መሆኑ ታወቀ
(መሠረት ሚድያ)- በርካታ የነዳጅ ማደያዎች ሕገወጥ ንግድ ላይ በመሰማራታቸው አዲስ አሠራር እስኪዘረጋ ድረስ በሚል አዲስ የነዳጅ ማደያ ለመክፈት ለሚጠይቁ ፈቃድ እንደማይሰጥ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ያስታወቀው ሚያዝያ 2016 ዓ.ም ላይ ነበር።
በወቅቱ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላ…



